1.     ዊንኤሮ ትዊከር(WinAeroTweaker)

ይህ መተግበሪያ በነፃ የሚሰራጭ ሲሆን በቀላሉ ካወረድነው በሗላ በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ልንጠቀምበት እንችላለን እንደሌሎች መተግበሪዎች ለመጫን ሒደት የለውም ይህ መተግበረያ በWindows 7, Windows 8, Windows 8.1, እንዲሁም Windows 10 ላይ መጠቀም እንችላለን




2.     ላንቺ (Launchy)

ላንቺ ለሁሉም Windowsን ለሚጠቀሙ ኮምፒውተሮች እንዲሆን ታስቦ የተሰራ መተግበሪያ ነው መተግበሪያው start menuን በመተካት start menu ሊሰጠን የሚችለውን ጥቅም በቀላሉ እንድናገኝ የሚያደርግ ነው ለምሳሌ፦ Documents, folders, bookmarks ሌሎችንም ጥቂት ቁልፎችን በመጫን በቀላሉ እንድናገኝ ያድረጋል Alt + Spaceን መጫን መተግበሪያውን ያስጀምረዋል

3.     ኦኮዞ ዲስክቶፕ (Okozo Desktop)

ኦኮዞ (Okozo) ድህረ-ገፅ ሲሆን ተንቀሳቃሽ የጀርባ ምስሎች (live wallpapers) ይገኙበታል ተንቀሳቃሽ የጀርባ ምስሎቹ በጣም የሚያምሩና ለኮምፒውተራቺን የተለየ የሚያምር ገፅታ ይሰጡታል. ከድህረ-ገፁ የተለያዩ ሰዓት፣ ያላቸው ሙዚቃ ማጫወት የሚችሉ እንደምርጫችን የተለያየ ነገር የታከለባቸው ተንቀሳቃሽ የጀርባ ምስሎችን (live wallpapers) በማውረድ ለምፒውተራችንን የተለየ የሚያምር ገፅታ መስጠት እንችላለን